=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ያለፈን ጊዜ ማስታወስና መጨነቅ፤የተከሰቱትን መጥፎ ነገሮች አስቦ ማዘን እብደትና ቂልነት እንዲሁም ነባራዊውን ህይወት መጉዳት እና ፍላጐትንም መግደል ጭምር ነው።ብልሆች ዘንድ ያለፈው ጊዜ መዝገብ እንደተዘጋ ይቀመጣል እንጂ ተከፍቶ አይነበብም።በመርሳት እስርቤት ውስጥ ይቆለፍበታል፤እንዳይወጣና ብርሃን እንዳያይ ተደርጐ ይታሰራል፤ጠንካራ በሆኑ ገመዶችም ይጠፈራል፤አልፏል አብቅቶለታልም።ሃዘን አይመልሰው፣ጭንቀት አያርመው፣ትካዜ አያስተካክለው፣መጠበብም አያኖረውም....ሞቷልና።በአላፊው ጊዜ ብዥታ ውስጥ አትኑር፤በጥላውም ስር አትቆይ፤ራስህን አድን።
√ ወንዝን ወደ ምንጩ መመለስ ትፈልጋለህ?
ፀሃይን ወደ መውጫዋ፣ህፃንን ወደ እናቱ ሆድ፣ወተትን ወደ ጡት፣እንባን ወደ ዓይን መመለስ ታስባለህን? አንተ ከአላፊ ጊዜ ጋር መኖርህ በሱም መጨነቅህ፣በእሳቱም መቃጠልህ፣በደጃፎቹም መጋደምህ የሚያስፈራ፣የሚያስደነግጥ እና የሚሰቀጥጥ ነገር ነው።
ያለፈን ጊዜ ደብተር ገልጦ ማንበብ ዛሬን ማጥፋት ነው፤ዛሬን አሽቀንጥሮ መጣል ነው።አሏህ በቁርአን ውስጥ ያለፉ ህዝቦችንና ስራዎቻቸውን በጠቀሰ ቁጥር «እነዚያ ያለፉ ህዝቦች ናቸው።» ብሎ ይቇጫል።ነገሩ ተፈፀመ አለቀም።የዘመንን በድን ማረድ ፋይዳ የለውም።የታሪክንም ኡደት ወደ ኋላ መመለስ አይጠቅምም።ወደ ትናንቱ የሚመለስ ሰው የተፈጨን ዱቄት መልሶ እንደሚፈጭ እና የእንጨት ፍሬን መልሶ እንደሚፈረፍር ሰው ነው።ድሮ ድሮ ትናንቱን አስቦ ለሚያለቅስ ሰው ሙታንን ከቀብሮቻቸው ለማውጣት አትሞክር ይባል ነበር።
ጥፋታችን ዛሬን መኖር አቅቶን ስለትናንት መጨነቃችን እና ውብ የሆኑ ቤቶቻችንን ትተን የተፈረካከሱ ህንፃዎችን መሻታችን ነው።የሰው ልጆች እና አጋንንት ሁሉ ያለፈውን ጊዜ እንመልስ ብለው ቢሰበሰቡ በፍጹፁም አይችሉም።ሰዎች ያለፈውን ጊዜ እያሰቡ መኖር የለባቸውም።ትናንትን እያስታወሱ መጨነቅም አይጠቅማቸውም።ነፍስ የሚነፍሰው ወደፊት፣ውሃም የሚፈሰው ወደፊት፣ቅፍለቶችም የሚጔዙት ወደፊት ነውና የህይወትን ስርአት አትጣስ!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|